Home

 

ግልጽ ደብዳቤ

PUBLIC STATEMENT

በቅርቡ የምንቀበለውን ታላቁን የጌታ ፆም (ዓቢይ ፆም) ምክንያት በማድረግ የርዕሰ አድባራት ለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሰበካ አስተዳደር ጉባኤ (Part 8 Claim በሚል በቀረበው ክስ ስማቸው በተከሳሽነት የተገለጸው) በይገባኛል ጥያቄው ምክንያት በቤተ ክርስቲያናችን ላይ የተከሰተውን ልዩነትና አላስፈላጊ ክርክር እልባት ለመስጠት በማሰብና ከልብ በመመኘት የሚከተለውን ግልጽ ማስታወቂያ ለሕዝበ ክርስቲያን ሁሉ ያስተላልፋሉ።

As we approach the Great Lent, the Parish Administration Council (the Part 8 Defendants as named in the attached Claim Form issued by the Claimants) wish to set out publicly their desire to resolve and bring to a conclusion the bitterness and division caused by the on-going litigation that relates to the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church of St Mary of Debre Tsion.

የሰበካ አስተዳደር ጉባኤው አባላት (ተከሳሾች/Part 8 Defendants) አሁን የሚታዩ የአስተዳደር ክፍተቶችን የሚያርም አዲስ የመተዳደሪያ ሕግ ተዘጋጅቶ በሥራ ላይ ቢውል የቤተክርስቲያኑን/የቻሪቲውን የወደፊት አስተዳደር የተቃና ያደርጋል የሚል እምነት አላቸው። አዲሱ የመተዳደሪያ ሕግ ቻሪቲውን ሕጋዊ አካልነት ያለው የበጐ አድራጎት ተቋም እንዲሆን ማድረግን የሚጨምር ይሆናል። ስምምነት በሚደረግበት የሥራ አፈጻጸም ዕቅድ መሠረት አዲስ የሰበካ አስተዳደር ጉባኤ አባላት (ባለ አደራዎች) ምርጫ ማከናወን የዚሁ ሒደት አካል ይሆናል።

The Part 8 Defendants believe that the future of our charity should involve putting in place a new constitutional document that provides robust governance arrangements. This may involve reconstituting the charity as a charitable incorporated organisation. As part of this process elections would be held within an agreed framework to elect new Trustees.

የሕግ ክርክሩን ያስጀመረው የከሳሾች (The Part 8 Claimants) የይገባናል ጥያቄ በአንቀጽ 10 (2) ላይ መሠረታዊ የሆነ ጥያቄ አቅርበዋል። የጥያቄውም ዝርዘር የእናት ቤተ ክርስቲያን ቅርንጫፍ ሆና አገልግሎት የምትፈጽም መሆኑን በሚገልጸው ክፍል ውስጥ የለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን በየትኛው ቅዱስ ሲኖዶስ እና ቅዱስ ፓትርያርክ የመንፈሳዊ አስተዳደር ሥልጣን ስር እንደሆነች እንዲወሰን ጥያቄ አቅርበዋል። ይኸውም፦

(ሀ) ኢትዮጵያ በሚገኘው ቅዱስ ሲኖዶስ እና በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ ወይስ

(ለ) በስደት በአሜሪካ በሚገኘው ቅዱስ ሲኖዶስ እና በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ወይስ

(ሐ) በማንም ስር አይደለችም

በሚል የቀረበ ነው።

The Claimants have, in their Claim Form commencing the litigation, raised a fundamental question in paragraph 10(2). of the Details of Claim about whether the Mother Church of which our church is described as a branch is operated either under the spiritual jurisdiction of:

(a) The Holy Synod in Ethiopia and His Holiness Patriarch Mathias, or

(b) The Holy Synod in exile in America and His Holiness Patriarch Merkorios, or

(c) no-one.

የሰበካ አስተዳደር ጉባኤው አባላት (The Part 8 Defendants) የለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ቅርንጫፍ ሆና አገልግሎቷን ስትፈጽም የቆየችው ኢትዮጵያ በሚገኘው ቅዱስ ሲኖዶስ እና በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ በምትመራው እንዲሁም በመንበረ ፓትርያርኩ ተቀምጠው የፓትርያርክነቱን ሥልጣን ይዘው ሲያስተዳድሩ በነበሩ ቀደምቶቻቸው ስትመራ በቆየችው እናት ቤተ ክርስቲያን ስር መሆኗን በጽኑ ያምናሉ።

The Part 8 Defendants firmly believe that the Mother Church of which our church is a branch is operated under the spiritual jurisdiction of the Holy Synod in Ethiopia and His Holiness Patriarch Mathias and his predecessors who held the office preside on the Patriarchate in Ethiopia.

ከሳሾች (Part 8 Claimants) የለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ኢትዮጵያ በሚገኘው ቅዱስ ሲኖዶስ እና በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ መንፈሳዊ አስተዳደር ስር የምትተዳደረው እናት ቤተ ክርስቲያን ቅርንጫፍ መሆኗን በይፋ ቢቀበሉ፣ ይህንኑም በሚቀጥሉት 7 ቀናት ውስጥ ቢያሳውቁ የልዩነት ምክንያት የሆኑ ጉዳዮችን በቀላሉ እልባት ለመስጠት፣ የዕርቅና የሰላሙን መንገድ ለመጀመር እንደሚቻል ተከሳሾች (Part 8 Defendants) እምነት አላቸው።

In order to bring matters to a conclusion and start on the path to reconciliation, the Part 8 Defendants ask the Claimants to publicly confirm within the next 7 days that they agree that the Mother Church of which our church is a branch is subject to the spiritual jurisdiction of the Holy Synod in Ethiopia and His Holiness Patriarch Mathias.

ከሳሾች (Part 8 Claimants) ከላይ የቀረበውን ሐሳብ መቀበላቸውን ቢያረጋግጡ ሁለቱም ወገኖች በአፋጣኝ ወደ ዕርቅ እና አንድነት ለመድረስ፣ ለቻሪቲውም አዲስ የአስተዳደር መዋቅር ለመዘርጋት፣ አላስፈላጊ እና እጅግ በጣም ውድ የሆነውን የሕግ ክርክር ለማስወገድ እንደሚረዳ ተከሳሾች (Part 8 Defendants) እምነት አላቸው።

If the Claimants are able to provide this confirmation, the Part 8 Defendants believe that the parties will be able to move quickly towards unity and reconciliation, putting in place a new governance structure for our charity and avoiding unnecessary and costly litigation.

የርዕሰ አድባራት ለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን

ሰበካ አስተዳደር ጉባኤ / ባለ አደራዎች

(Part 8 Claim ተከሳሾች)

The Parish Administration Council / Trustees of

Ethiopian Orthodox Tewahdo Church

St Mary of Debre Tsion, London

(Defendants in the Part 8 Claim)

የካቲት ፯ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. 14th February 2017